Uncategorized – Gaber Support in North America

ጋበርን በጨረፍታ
በወረዳችን ኧዣ ስር ሰደው የሚገኙ በርካታ ችግሮችን በመለየት እንዴት መቅረፍ ይቻላል በሚለው ላይ ከበርካታ ተወላጆች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶች ከተደረጉ በሗላ የበጎ አድራጎት ድርጅት መመስረት እንደሚሻል ታመነበት::

በዋናነት የበጎ አድራጎት ድርጅት የተመረጠበት ምክንያት:

ችግሮቹ የበዙ በመሆናቸው ባለን ውስን አቅም ብዙሃኑን የሚያሳትፍና ብዙ ዓይነት ስራዎችን ጎን ለጎን መስራት የሚያስችል አደረጃጀት በመፈለግ:

እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ ተወላጆች ተሳታፊ እንዲሆኑ :  የዓባልነት ክፍያ በመፈፀም ገቢ እዲያስገኙና ቀጣይነት እንዲያረጋግጡ በማሰብ

ባለ ሀብቶች በገንዘብና ሙያተኞች በየሙያቸው በመደራጀት ችግሮችን ለመፍታት ወደ ሗላ እንደማይሉ ተስፋ በማድረግ

ከትላልቅ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች : ከምርምርና የመንግስት ተቋሟት የዕውቀትና የገንዘብ ድጋፍ ሊገኝ እንደሚችል በማመን ነበር::

በዚሁ መሠረት ጋበር የበጎ አድራጎት ድርጅት ነሓሴ 17 ቀን 2014 ዓ.ም. በመዝገብ ቁጥር 6365 በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተመዘገቦ ሕጋዊ ሰውነት አገኘ::

ጋበር በአንድ ዓመት ተኩል እድሜው ከኧዣ ወረዳ አስተዳደር ጋር በመተባበር ያከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራት:

በአዲስ አበባ ነዋሪ ከሆኑ ተወላጆች ጋር በጣም ብዙ የግንዛቤ ማስጨበጫና የገቢ ማሰባሰብያ ስብሰባዎችን አካሄዷል : በማካሄድም ላይ ይገኛል::

በወረዳችን ችግሮች ላይ ያተኮረ ውይይት ከወረዳውና ከአገና ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ጋር አድርጓል:: ችግሮቹን እጅ ለእጅ ተያይዘን ለመፍታት ቁርጠኛነት መኖሩን አረጋገጠ::

የጋበር ቢሮና የበላይ አመራርን (አንድ ዋና ስራ አስኪያጅ : አንድ የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊና አንድ የሞኒተሪንግና መምርያ ኃላፊ) አዋቀረ::

በትምህርት ላይ ያሉትን ችግሮች ለመለየት በከፍተኛ ባለሙያ በመታገዝ ተማሪዎችን : መምህራንን : የትምህርት አመራርን : የወላጅ ኮሚቴን ያካተተ ሰፊ ጥናት አካሄዷል::

ሁለት ጊዜ ከአገና ከተማ አስተዳደርና ከ28ቱ የገበሬ ማህበራት ተወካዮች ጋር በወረዳችን ስር ሠደው  በሚገኙ ችግሮችና መፍቻ ዘዴዎቻቸው ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውይይት አካሄዷል::

በሰሜን አሜሪካ ከሚኖሩ የኧዣ ተወላጆች ጋር ግንኙነት በመፍጠር ጋበር ሠፖርት ግሩፕ ኖርዝ አሜሪካ የተሠኘ ህጋዊ የበጎ አድራጎት ድርጅት ተቋቁሞ አባላት በማሰባሰብና የአባልነት ክፍያ በመሠብሰብ ላይ ይገኛል:: በአውሮፓ ከሚኖሩ ተወላጆች ጋርም ተመሳሳይ አደረጃጀት ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ ነው::

በኣርቲስት አብርሃም ወልዴ እና በባለቤቱ ወ/ሮ ማክዳ ኃ/ሚካኤል  በተደረገለዠት የብር 250 ሺህ ልገሳ 450 የብርድልብሶች ገዝቶ ለወገኖቻችን አድሏል::

የጋበር ቴሌግራም ተከታዮች ቁጥር ለማብዛትና ለተማሪዎች መጻህፍት ማሳተሚያ ገንዘብ ለማሰባሰብ በተደረገ ከፍተኛ ጥረት በርካታ ተከታዮች ማፍራትና በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ ከሚኖሩ ተወላጆችና ቸር ኢትዮጵያውያን በሚሊዮኖች ገንዘብ ማሰባሰብ ተችሏል::

*በወረዳው ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ላሉ ሁሉም ተማሪዎች ለ6 የትምህርት ዓይነቶች አንድ መጽሃፍ ለ5 ተማሪዎች መጠቀምያ እንዲሆን አሳትሞ አድሏል::

በወረዳው ለሚገኙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በርካታ የማጣቀሻ መጽሃፍት በእርዳታና በግዥ አግኝቶ አከፋፍሏል

በወረዳው ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ሁሉም ሴት ተማሪዎች ለአንድ ዓመት የሚያገለግል የንጽህና መጠበቂያ አስመርቶ አከፋፍሏል::

በወረዳው ለሚገኙ 2ኛ ደረጃ እና ለአገና ኢንደስትርያል ኮሌጅ ተማሪዎች በባለሙያ የተዘጋጀ የጥናት ሠነድ መሠረት በማድረግ በስነምግባርና በእውቀት የሚበለጽጉበትን ምክርና ውይይት በየትምህርት ቤታቸው በመገኘት አካሄዷል::

በአንድ ቀን ከመላው የኧዧ ነዋሪዎች ጋር አገር ቤት በየገበሬ ማህበራቸው በመገኘት በችግሮችና መፍቻ ዘዴዎች ላይ የግማሽ ቀን ውይይት አካሄዷል:: በውይይቱም የኧዣን መሠረታዊ ችግሮች ከህብረተሰቡ በግለጽ የተነሱ ሲሆን ለመፍትሄውም ህብረተሰቡን የሚያስተባብሩ : በኣርኣያነታቸው እምነት ያተረፉ ዓባላት ያካተተ ኮሚቴ በሁሉም የቀበሌ ገበሬ ማህበር እንዲቋቋም ተወስናል:: የኮሚቴ ኣባላት ምርጫ የተጠናቀቀ ሲሆን ኃላፊነታቸውን በተመለከተም በቅርቡ የጋራ ውይይት ይካሄዳል::

የወረዳችንን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉና ብሎም ከፍ የሚያደርጉ በቦርድ ዓባላት የሚመሩ 9 ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች ተዋቅረው ወደ ስራ በመግባት ላይ ይገኛሉ::

የ2015 የትምህርት ዘመን አገር አቀፍ ፈተና ከተፈተኑ ተማሪዎች ጋር ውይይት በማድረግ በቀጥታ ለዩኒቨርስቲና ለሪሜዳል ትምህርት ያለፉትን በትምህርታቸው እንዲበረቱ መክሯል : በባለሙያ የአጠናን ዘዴዎችን አስረድቷል:: የማበረታቻ ስጦታም አድርጓል:: የተቀሩት ተማሪዎችም አገና ኢንዱስትርያል ኮሌጅ ገብተው ስልጠና እንዲወስዱ የቴክኒክ ሙያን ዘርፈ ብዙ ጥቅም አስረድቷል:: ወጣቱ በተለያዩ ሙያዎች በመሳተፍ በአካባቢዬም ሠረቼ ያልፍልኛል የሚል ስሜት እንዲያዳብር ሰፊ ቅስቀሳ ተደርጓል::

በውኃና መስኖ ላይ ጥናት የሚያደርግ የከፍተኛ ሙያተኞች ቡድን ተቋቁሞ ስራ ጀምሯል::

በኧዣና በቤተሰብ ስም የተቋቋሙ ዕድሮች በርካታ ህዝብ ያቀፉ ስለሆኑ ጋበርን የሚደግፉበት ዘዴ ለመቀየስ እድሮችን በተመለከተ አኩሪ ተግባር ከፈፀመው የኧዣ ዕድሮች ህብረት ቢዝነስ አክስዮን ማህበር የቦርድ አመራር ጋር ገንቢ ውይይት አካሄዷል::

ክብርና ምስጋና በችግር ላይ የሚገኙ ወገኖቻችሁን ለመርዳት የአቅማችሁን ለምታደርጉ ሁሉ ይሁን::

የጋበር ኣባል ይሁኑ : በገንዘብዎና በሙያዎ ጋበርን በመርዳት እዳዎን ይከፊሉ ::

አቶ ኮሬ ባዌ፤ የጋበር በጎ አድራጎት ድርጅት ሊቀመንበር